የጡት ካንሰር
የጡት ካንሰር ግንዛቤዎን ያዳብሩ
በበለፀጉ አገሮች የወቅቱ የጡት ካንሰር እስታትስቲክስ እንደሚያሳየው ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል አላት፡፡
ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ አስጊ ሁኔታዎች
የዕድሜ መግፋት፡- በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል እድሜ ሲጨምር ይጨምራል፡፡ሁኔታው በየ10 ዓመቱ በእጥፍ ይጨምራል፡፡
ቀድሞ ለአካለ መጠን መድረስና ዘግይቶ ማረጥ፡- ቀደም ካለው የወር አበባቸው ማየት በሚጀምሩ ሴቶችና ከ55 ዓመታት በኃላ ዘግይተው ማረጥ በሚጀምሩ ሴቶች ላይ በጡት ካንሰር የመጠቃት እድሉ ይጨምራል፡፡
ጡት አለማጥባት፡- አንዲት ሴት አንድ ወይም ሁለት ልጅ ጡት ካጠባች ሴት ይልቅ ምንም ያላጠባች ሴት የበለጠ በጡት ካንሠር የመያዝ ዕድል አላት፡፡
ከመጠን ያለፈ ክብደት፡- እድሜ በጨመረ ጊዜ (ድህረ ማረጥ) በከፍተኛ ሁኔታ ክብደት ከጨመረ ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድል ይጨምራል፡፡እንደዚሁም ከፍተኛ ቅባት ያለው ምግብ በመመገብና በጡት ካንሰር በመያዝ መካከል ግንኙነት አለ፡፡
አልኮል መጠጣት፡- አንዳንድ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከሆነ አልኮል በመጠጣትና በጡት ካንሰር መካከል ግንኙነት አለ፡፡በከፍተኛ ሁኔታ አልኮል የሚጠጡ ሴቶች ይልቅ ለጡት ካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡
የሆርሞን ሕክምና፡- (በ5 ዓመት ጊዜ) የሆርሞን ሕክምና ባደረጉ መጠን ለጡት ካንሰር መጋለጥ በጥቂቱ ይጨምራል፡፡የሆርሞን ሕክምና ለጡት ሕመም ይዳርግና አነስተኛ ካንሰር መኖሩን ለማረጋገጥ በቀላሉ እንዳይቻል ያደርጋል፡፡
የቤተሰብ ታሪክ፡- ከ10 ሴቶች አንዷ ከቤተሰብ በወረሰችው የዘረመል ደንበወጥነት ካለ ለጡት ካሰር የመጋለጥ እድሏ ይጨምራል፡፡
በዓለም አቀፍ የሕክምና ባለሙያዎች የጡት ካንሰር ገና ከጅማሬው ለማወቅ 3 ደረጃዎች ተጠቁመዋል፡፡
ከ20 ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ እራስን መመርመር
- ከ20 ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ እራስን መመርመር
- እስከ 40 ዓመት በየ3 ዓመቱ እና ከ40 ዓመት በኋላ በየዓመቱ በብቁ የሕክምና ባለሙያ የሀኪም ቤት የጡት ምርመራ ማድረግ
- በ50 ዓመትና ከዚያ በኋላ በየ3 ዓመቱ የጡት ራጅ መነሳት
ጡትን በራስ የመርመሪያ መንገዶች
ጡትን በመደበኛው ሁኔታ በራስ መመርመር የጡትን ጤናማነት እንዲሰማ እና እንዲያዩት ስለሚያስችሎት ማንኛውም ለውጥ ካለ በጊዜ ይረዱታል፡፡ጡትን እራስ ለመርመርም
አንደኛ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ጡትዎን ለመመርመር ቀጥ ብለው ይቁሙ፤ ጡትዎን በመስታወት ይመልከቱ፤በሁለቱም ጡቶች ላይ የቅርፅ እና የመጠን ለውጥ እንዳለ ያስተውሉ፤ ማንኛውም ዓይነት የቆዳ ቀለም ወይም ውጫዊ አካል ለውጥ ካለ ይመርምሩ፤ ክንድዎትን ዝቅ በማድረግ የጡትዎን ጫፍ በአውራ ጣትና በጣት መካከል አድርገው በመጭመቅ ከጡት ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ ይመርምሩ
ሁለተኛ፡- ቀጥ ብለው ከመስታወት ፊት ለፊት ቀመው በቀኝ እጅ ጡቶዎችን ይዳስሱ፤በሁለተኛው፤በሶስተኛውና በአራተኛው፤የእጅ ጣቶች ጠንከር ያለ፤ ለስላሳ አነካክ በመንካት የውስጥ ህብረዋስ (ቲሹ) እና የቆዳ ውስጥ ህብረ ህዋስ እስኪሰማዎ ድረስ ጣቶችዎን ዘርግተው ጡቶችዎን በሰፊው ጫን ጫን ይበሉዋቸው፡፡ጡቶችዎንና ብብትወፐ አካባቢ በደንብ እንዲፈትሹ ያረጋግጡ፡፡
ሶስተኛ፡- ቀጥሎ ግራ ትከሻዎት ላይ ትንሽ ወይም የታጠፈ ፎጣ በማድረግ በጀርባ ይንጋለሉ፡፡ግራ እጅዎን ከጭንቅላት በላይ ያንሱ፡፡ግራ ጡትዎን ለመፈተሸ የቀኝ እጅ አንደና፤ሁለተኛ፤ሶስተኛ ስና አራተኛ ጣቶች ጫፍ ለስላሳ ክፍል ይጠቀሙ፡፡የውስጥ ሕብረ ሕዋስና የቆዳ ውስጥ ህብረ ሕዋስ እስኪሰማዎት ድረስ በደንብ ይጫኑት፡፡እንደዚሁም በጡት ዙሪያ የላይኛውን አካባቢና የብብትዎ አካባቢ መካከል ያለውን ቦታ በደንብ ይፈትሹ፡፡ግራ እጅዎን በመጠቀም በቀኝ ጡት ላይ ተመሳሳዩን ይድገሙ፡፡ ማንኛውም አይነት ለውጦች፤ደንበወትነቶች ወይም ፈሳሾች ካሉ በተቻለ ፍጥነት ሀኪምዎን ያማክሩ፡፡ጡታቸውን በየጊዜው እንዲመረምሩ ጓደኞችዎንና ቤተሰብዎን ያበረታቱ፡፡ለጡት ካንሰር አደጋ ለሚያጋልጥ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ ከሆኑ እባክዎን በተደጋጋሚ ጡትዎን በመመርመር ሐኪምዎን ያማክሩ፡፡
















