• An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
 

ማቲዎስ ማነው?

ማቲዎስ ከእናቱ ወ/ሮ አምሳለ በየነና ከአባቱ አቶ ወንዱ በቀለ ሰኔ 9 ቀን 1991 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ፡፡ የሁለተኛ ዓመት ልደት በዓሉን ባከበረ ጥቂት ቀናት ውስጥ በቤተሰቡ ዘንድ በፍፁም ያልተጠበቀ የጤና ችግር አጋጠመው። በጥሩ ሁኔታ ዕድገቱን ጠብቆ በመኖር ላይ የነበረውና አንድም ቀን ህመም አጋጥሞት የማያውቀው ማቲ በተደረገለት የጤና ምርመራ በደም ካንሠር ህመም መያዙ ታወቀ።


ዝርዝር ንባብ...
 
Amharic (Ethiopia)English (United Kingdom)
PDF ፕሪንት ኢሜይል

ማቲዎስ ማነው?

ማቲዎስ ከእናቱ ወ/ሮ አምሳለ በየነና ከአባቱ አቶ ወንዱ በቀለ ሰኔ 9 ቀን 1991 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ፡፡ የሁለተኛ ዓመት ልደት በዓሉን ባከበረ ጥቂት ቀናት ውስጥ በቤተሰቡ ዘንድ በፍፁም ያልተጠበቀ የጤና ችግር አጋጠመው። በጥሩ ሁኔታ ዕድገቱን ጠብቆ በመኖር ላይ የነበረውና አንድም ቀን ህመም አጋጥሞት የማያውቀው ማቲ በተደረገለት የጤና ምርመራ በደም ካንሠር ህመም መያዙ ታወቀ።


ምንም እንኳን በአገራችን የካንሠር ህመምን በአግባቡ ለማከም የሚያስችል አመቺ ሁኔታ የሌለ ቢሆንም ቤተሰቦቹ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምናው እንዲቀርብ የተጠየቁትን መድሐኒቶች በሙሉ ከውጭ አገርና ከአገር ውስጥ በውድ ዋጋ በማቅረብ ከአጠገቡ ሳይለዩ በቅርቡ ሆነው በማስታመማቸውና ሐኪሞቹም የተቻላቸውን ሁሉ በማድረጋቸው እንደ ማቲዎስ ተሟልቶለት የታከመ የለም እስከመባል ተደርሷል። ለ22 ወራት ህክምናውን በአግባቡና በጥሩ ሁኔታ በመከታተል ላይ እያለና ከጥቂት ወራት በኋላ ህክምናውን ጨርሶ ያቆማል ተብሎ በጉጉት ሲጠበቅ ህመሙ እንደገና ማገርሸቱ ታወቀ።

በካንሠር ህክምና ሂደት ውስጥ የበሽታው ማገርሸት ህመሙን አክሞ ለማዳን የሚደረገውን ጥረት የበለጠ ውስብስብና ውጤቱንም አነስተኛ ያደርገዋል፡፡ ህክምናው ውድ ከመሆኑም በላይ በአገር ውስጥ የማይሰጥ በመሆኑ ማቲዎስ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም በሆስፒታሉ የሐኪሞች ቦርድ ተወሰነ። የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተው በመጨረሻ ላይ በመላው ዓለም የታወቀውና በዋሺንግተን ዲ.ሲ. አሜሪካ የሚገኘው ብሔራዊ የካንሠር ኢንስቲትዩት ማቲዎሰን ተቀብሎ  የቦን ማሮው ህክምና ለማድረግ ተስማማ፡፡ በጉዞውም የማቲዎስ እናትና ወንድም አብረውት እንዲሄዱ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎችና ዋሺንግተን የሚያርፉበት ቤት ተዘጋጅቶላቸው የሚሄዱበት ጊዜ በጉጉት እየተጠበቀ መስከረም 13 ቀን 1996 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያለ ከዚህ ዓለም ተለየ።

በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሲደረግ የነበረው የተሟላ ጥረት ምንም እንኳን ማቲን በህይወት ለማቆየት ባያስችልም ጥረቱ ሳይቋረጥ ተጠናክሮ ሌሎቹን ወገኖቻችንን ለመርዳት እንዲውል የማቲ ቤተሰቦችና ወዳጆች 15 ሆነው ይህንን ሶሳይቲ አቋቁመው በስሙ እንዲጠራ አድርገዋል።
 
 

በራስዎ ተጠቃሚ ስም እና የሚስጥር ኮድ ይግቡ

ማን መስመር ላይ አለ?

አለን 6 እንግዳ መስመር ላይ
 
 
Joomla 1.5 Templates by Joomlashack